ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የቤቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ 01-2026/27
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማካካሻነት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተቁ | የንብረቱ ዓይነትና የሚሰጠው አገልግሎት | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ | የቦታው ስፋት በካ.ሜትር | የካርታ ቁጥር | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ||
| ከተማ | ክ/ከተማ | ቀበሌ/ወረዳ | ||||||
| 1 | የታሸገ ውሃ ማቀነባበሪያ እና መጋዘን | ሸገር | ሰበታ | አዋስ | 6000 | WLBEN/7679 | ሆሳዕና | 28,000,000.00 |
| 2 | መኖሪያ ቤት G+4 ህንፃ | አዲስ አበባ | ኮልፌ ቀራኒዮ | ወረዳ 03 | 250 | K04/1/47/338/389/3854/02 | በቅሎቤት | 30,000,000.00 |
| 3 | መኖሪያ ቤት | ጎንደር | ሳንጃ | 01 | 340 | 00 831 | ጎንደር | 1,400,000.00 |
| 4 | መኖሪያ ቤት | አዳማ | – | 01 | 180 | 736467/98 | አዳማ | 5,000,000.00 |
| 5 | መኖሪያ ቤት B+G+4 ህንጻ
|
አዲስ አበባ
|
ቂርቆስ | ወረዳ 01 | 133.35ካሜ x 4
114.01ካሜ x 1 |
000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 AA | ስታዲየም
|
65,000,000.00
|
| 6 | መጋዘን | ሸገር | ገላን | ገላን ቀበሌ | 6300 | BMG/K/L/I/TA/2014 | ወሎሰፈር | 95,000,000.00 |
የጨረታው ደንቦች፡-
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በባንኩ ስታዲየም ቅ/ፍ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና ግሎባል ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ /ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ ላይ 7ኛ ፎቅ/ በአካል በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /ፎርም/ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡:
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ በመቶ) በገንዘብ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ /ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ/ በአካል በመቅረብ እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ መሆን አለበት። ይህንንም በግልጽ ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች ድርጅት ከሆነ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት፣ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በ30 /ሠላሳ / ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ከባንኩ ጋር የሽያጭ ውል መግባት አለበት፡፡ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብም ካሸነፈበት ገንዘብ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ማሸነፉ ከተገለጸለት በኋላ እስከ 30ኛው ቀን ድረስ አስፈላጊውን የሽያጭ ውል የማይፈጽም ከሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ይሆናል።
- በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ውሳኔ እንዳገኘ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል የትብብር ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ለመንግስት ማንኛውም ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ ንብረት በማስተላለፍ ሂደት የሚኖር ክፍያ እና ሌሎች ማንኛውንም ክፍያዎች ገዢው ይከፍላል፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 26 ቀን 2018 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት 7ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የስብሰባ አደራሽ ይከፈታል፡፡
- መረጃ እና የንብረቶቹን አጠቃላይ ሁኔታ ማየት የሚፈልግ ተጫራች ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በስልክ ቁጥር 0115 58 12 04 ወይም 0115 31 80 97 በመደወል እና ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት 2፡00 – 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 – 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 – 6፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ መጎብኘት ይችላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለጋራ ስኬታችን!
