አማራ ባንክ አ.ማ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው 216/92 መሠረት በእዳ ማካካሻነት የወረሳቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
አማራ ባንክ አ.ማ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የመኖሪያ ቤቶች የሽያጭ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አባ/ንፋማመ/02/18
አማራ ባንክ አ.ማ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው 216/92 መሠረት በእዳ ማካካሻነት የወረሳቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ሙሉ ስም | የንብረቶቹ ዓይነትና አገልግሎት | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | ንብረቶቹ የሚገኝበት አድራሻ | የጨረታ መነሻ
ዋጋ |
ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ | |||
| ከተማ | ክ/ከተማ | ወረዳ | ልዩ ቦታ | |||||||
| 1 | አቶ ሞገስ ሲሳይ በለው | መኖሪያ ቤት 253ካ.ሜ | 150ካ.ሜ | ይከ/001/1228/011 | አስከተማ | – | 01 | ጋዝጊብላ | 1,037,951.89 | አስከተማ ቅርንጫፍ |
| 2 | አቶ ይገረም ስመኘው ፀጋዬ | መኖሪያ ቤት | 200 ካ.ሜ | K/09339 | ደ/ማርቆስ | – | 01 | ቀበሌ 09 | 3,328,941.09 | መንቆረር ቅርንጫፍ |
| 3 | አቶ ከኛወዲያ ላቀው ሃብተመስቀል | መኖሪያ ቤት | 200ካ.ሜ | ል/ቀማ/ቤታዊ/884/15 | አርባምንጭ | ሲቃላ | ወዜ | ድልፋና | 5,186,901.56 | ሴቻ ቅርንጫፍ |
| 4 | ፋርሚያ አግሪ ግሮው ኃ/የተ/የግ/ማህበር | መኖሪያ ቤት | 200ካ.ሜ | SUL/2292/12
|
ሱሉልታ | ሸገር | አባገዳ | ቀበሌ01 | 5,362,769.38 | ዋና መስሪያ ቤት 20ኛ ፎቅ |
| 5 | ፋርሚያ አግሪ ግሮው ኃ/የተ/የግ/ማህበር | መኖሪያ ቤት | 200ካ.ሜ | SUL/2293/12 | ሱሉልታ | ሸገር | አባገዳ | ቀበሌ 01 | 5,362,769.38 | ዋና መስሪያ ቤት 20ኛ ፎቅ |
የጨረታ መመሪያዎች
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሂሳብ ቁጥር ETB1756800010001 የማይመልስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ለገሃር በሚገኘው በዋናው መስሪያ ቤት 20ኛ ፎቅ ንብረትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ፣ አስከተማ ቅርንጫፍ፣ሴቻ ቅርንጫፍ፣ መንቆረር ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ዘወትር በስራ ሰዓት ከነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታዉን መነሻ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የአማራ ባንክ ቅርንጫፎች በባንኩ ስም ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ በማሰራት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት አስፈላጊዉን መረጃ በማሟላት ከባንኩ ጋር የሽያጭ ዉል መፈራረም ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ ውል በተዋዋለ በ15 ቀናት ውስጥ ዋጋውን አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፣ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በ5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተ.ቁ1 በተጠቀሱት አድራሻዎች በተመሳሳይ ጊዜ እና ሰዓት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከንብረቱ ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር፣ እንዲሁም የስም ዝውውር እና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎችን ይከፍላል፡፡
- ንብረቶችን በሥራ ሰዓት በፕሮግራም መጎብኘት/ማየት ይቻላሉ፡፡
- በባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሰረት የሚፈለገውን መስፈርት አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ 50% ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ 011-558-2660 መደወል ይችላሉ::
አማራ ባንክ አ.ማ ከባንክ ባሻገር!
