ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 ፣ 216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሐራጅ ማስታወቂያ
ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 ፣ 216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋሰትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም
|
የንብረት አስያዥ ስም | ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት | አበዳሪው ቅርንጫፍ | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ
|
የጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት እና ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ
|
ጨረታው የወጣው | |||||||
| ከተማ፣ ክ/ከ/ ወረዳ/
ቀበሌ |
የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር | የቦታ ስፋት በካ.ሜ/ሄክ | |||||||||||||
| 1 | ወ/ሮ ሀዊ አዱኛ ሳቦቃ | ተበዳሪው | መኖሪያ ቤት | ቦሴት | አዳማ ከተማ፣ቦኩ ሸነን ክ/ከተማ፣ሃሮሬቲ ወረዳ | OR13001Ad141/2011 | 105 | 4,675,846.33 | በ05/01/2019 ዓ.ም ከ4፡00-5፡00 ኦሮሚያ ባንክ፣ ቦሴት ቅርንጫፍ ውስጥ | ለአራተኛ ጊዜ | |||||
|
|
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም | የተሽከርካሪው አይነት፣የሚገኝበት አድራሻ፣የሰሌዳ ቁጥር እና የሻንሲ ቁጥር | የጨረታው መነሻ ዋጋ | የጨረታው ቀን እና ሰዓት | ጨረታው የወጣው | |||||||||
| የመኪናው አይነት | የሚገኝበት አድራሻ | የሰሌዳ ቁጥር | የተሰራበት ዘመን | ሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | ||||||||||
| 2. |
ሳንተን ጀነራል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማ |
ተበዳሪው |
ቶዮታ ላንድ ክሩዘር ደብል ጋቢና ፒካፕ (ቀረጥ አልከፈለም) | ሰንጋ ተራ አከባቢ የሚገኘው የባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
አአ-03-B23429 |
2020 |
JTEBB7100B012958 |
1HZ-0947459 |
11,500,000 | ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00-5፡00 ሰዓት በዋና መስሪያ ቤት |
ለሶስተኛ ጊዜ |
||||
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/ሲ.ፒ.ኦ በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል፡፡ ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ የጨረታ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ቀረጥና ታክስ እና ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል፡፡ ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል፡፡
- በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው ተሽከርካሪ ከቀረጥና ታክስ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ሲሆን እስከ ሰኔ 01 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚፈለግበት ቀረጥና ታክስ ብር 4,732,379.13 ሲሆን የተሽከርካሪው የጨረታ መነሻ ዋጋ ያልተከፈለ ቀረጥና ታክስን አይጨምርም፡፡
- ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 እና ወይም 251919749020 ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት፣ ለተራ ቁ.1 በ 022-112-6635/45/69 ኦሮሚያ ባንክ ቦሴት ቅርንጫፍ፣ ለተ.ቁ.2 በ011-6-59-14-21/08-82 ኦሮሚያ ባንክ ለም ሆቴል ቅርንጫፍ፣ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኦሮሚያ ባንክ
