Tender Detail

Tender Details


ጂኤስ የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመርካቶ አካባቢ ለከፍተኛ ንግድና መኖሪያ አገልግሎት የሚውል 2B+SB+G+9 የቅይጥ ሕንፃ (Mixed-Use Building) በ 4111.73 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ትልቅ ሶሰት ብሎክ ያለው ህንፃዎችን በመገንባት ላይ ያለ አክሲዮን ማህበር ነው፡፡


ለግንባታ እቃ አቅራቢ ድርጅቶች የወጣ ጨረታ

ጂኤስ የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመርካቶ አካባቢ ለከፍተኛ ንግድና መኖሪያ አገልግሎት የሚውል 2B+SB+G+9 የቅይጥ ሕንፃ (Mixed-Use Building) በ 4111.73 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ትልቅ ሶሰት ብሎክ ያለው ህንፃዎችን በመገንባት ላይ ያለ አክሲዮን ማህበር ነው፡፡

ግንባታው አጠቃላይ የማጠናቀቂያ ሥራ እየሰራ መሆኑን ተከትሎ  ከዚህ በታች በተጠቀሱት የማጠናቀቂያ ፊኒሽንግ/finishing/፣ የኤሌክትሪክ/electrical/ እና የሳኒተሪ/sanitary/ ቁሳቁሶችን/materials/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።

                  ሀ. የማጠናቀቂያ ቁሳቁሶች (Finishing Materials)

  • የማርብል (Marble)፤ግራናይት/Granite/፤ዝኮሎ/skirting/
  • የጂፕሰም ቦርድ እና የተሟሉ የአሉሚኒየም እና የፓነል መለዋወጫዎች
  • የውስጥ እና የውጭ በር/መስኮት መግጠሚያዎች (Aluminum Profiles & Tempered Glass)
  • ጥራት ያላቸው የውስጥ እና የውጭ ቅብ ቀለሞች (Paints & Primers)
  • ቱቦላሬ ብረቶች/RHS and CHS/ እና ሌሎችም

ለ. የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶች (Electrical Materials)

  • የተለያዩ መጠን ያላቸው የኃይል እና የመብራት ኬብሎች (Wires & Cables)
  • ኮንዲዩቶች/conduits/
  • ዋና እና ንዑስ የኤሌክትሪክ ስርጭት ሳጥኖች (Main & Sub Distribution Boards / Breakers)
  • ዘመናዊ የመብራት ገጠማዎች፣ የሊድ (LED) መብራቶች፣ ስዊቾች እና ሶኬቶች
  • የደህንነት፣ የካሜራ (CCTV) እና የእሳት አደጋ ማስጠንቀቂያ/Fire alarm/ ኬብሎችና መለዋወጫዎች እና ሌሎችም

ሐ. የሳኒተሪ ቁሳቁሶች (Sanitary Materials)

  • የውሃ ማስተላለፊያ እና የፍሳሽ ቱቦዎች (PPR, HDPE, PVC Pipes & Fittings)
  • ዘመናዊ የሽንት ቤት ገንዳዎች፣ የእጅ መታጠቢያዎች፣ ሻወሮች እና የውሃ ቧንቧዎች እና ሌሎችም

በመሆኑም በየዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጠየቁትን ቁሳቁሶች በጥራት እና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራጮች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ከነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ነሐሴ19 ቀን 2018 ዓ.ም 9፡00 ሰዓት ድረስ ከማህበሩ ፅ/ቤት አድራሻ መውሰድ ይችላሉ፡፡

 

ተጫራቾች ሕጋዊ ሰነዶቻቸውን ፤ የዋጋ ሰነዶቻቸውን ዋና እና ኮፒ ለየብቻ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም  ጠዋት 4፡00 ይከፈታል፡፡

የማህበሩ አደራሻ ፡ በመርካቶ ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ ጂኤስ የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን            ማህበር ግንባታ ቦታ በሆነው አባ መላ የገበያ መዕከል 3 ፎቅ 

ማሳሰቢያ፦ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡– 0911438371/0927357195/0911627293 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

Save Tender