የተማሪ መጽሐፍት ከወላይታ ሦዶ ወደ ጂንካ ማጓጓዝ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የአሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የተማሪ መጽሐፍት ከወላይታ ሦዶ ወደ ጂንካ ለማጓጓዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
በሁሉም መስኮች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ፍቃድ ያሳደሱ ። የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NUMBER) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት (VAT) ማስረጃ ያለው ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የታክስ ኪሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ። የንግድ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው ፤እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000ብር ማቅረብ አለባቸው።
ከላይ የተገለጹትን ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ በነፃ ከኣሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ከግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 ቀርቦ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። የጨረታውን ሰነድ በ16ኛው አስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡30 ሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚያው ቀን 8፡30 ሰዓት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው ሲከፈት የተጫራቾች ያለመሟላት የጨረታ ሂደቱን እያስተጓጉልም።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 09 16-13-59-77
በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የአሪ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
