Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2019 የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉ፤- የጽሕፈት፣ የጽዳት መሳሪዎች፣ አላቂ የጽሕፈት ቤት እቃዎች፣ የህትመት ስራዎችን ቋሚ የመስሪያ ቤት መሳሪዎች የተለያዩ የምግብ አይነቶች እና ጊባቶቸ የደንብ ልብሶች፣ የግንባታ እና የእድሳት እቃዎች፣የኤለክትሮኒከስ እቃዎች፣ የተለያዩ ሞተር ሳይከሎች፣ ጀነሬተሮች እና የሞተር


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በ2019 የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉ፤- የጽሕፈት፣ የጽዳት መሳሪዎች፣ አላቂ የጽሕፈት ቤት እቃዎች፣ የህትመት ስራዎችን ቋሚ የመስሪያ ቤት መሳሪዎች የተለያዩ የምግብ አይነቶች እና ጊባቶቸ የደንብ ልብሶች፣ የግንባታ እና የእድሳት እቃዎች፣የኤለክትሮኒከስ እቃዎች፣ የተለያዩ ሞተር ሳይከሎች፣ ጀነሬተሮች እና የሞተር ሣይክሎች ጥገና የተለያዩ የሞተር ሳይከሎች እና የመኪና ጎማዎችን ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እና ግዴታዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የተጫራቾች መስፈርት ግዴታዎች
1. ጥራት ያላቸውን እቃዎች ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው።
2. በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ የምችሉ።
3. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የግዢ ደንብ እና መመሪያ የሚያከብር::
4. የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እና የ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ፍቃድ ያላቸው፡፡
የ2018 ዓ.ም ግብር ያልከፈሉ እና ለ 2019 ንግድ ፈቃዳቸውን ያላደሱ ከሆነ ከ ገ/ባ/ጽ/ቤት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
6. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን እና ማቸኑ (cash register machine) መኖሩን የሚያሳይ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የመጨረሻውን ወር የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያወራረደበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ለእያንዳንዳቸው 20,000ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል ወይም ከተደራጁ ከአንድ አመት በታች መሆኑን የሚገልጽ ድጋፍ ደብዳቤ ካደራጃቸው የመንግስት አካል ህጋዊ ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት ውል ከመፈራረሙ በፊት የሚገዙ እቃዎችን ናሙና በድርጅቱ ማህተም አስደግፈው ማቅረብ የሚችሉ።
9. የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 500 ብር በመክፈል ከማ/ወ/ገ/ባ/ጽ/ቤት
10. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ ማስገባት ይቻላል።
11. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን እና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ በቀን1/13/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰአት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በማስታወቂያ የተነገረ የመከፈቻ ቀን የእረፍት ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል ።
12. ጨረታው በተባለበት ቀን እና ሰአት ገብቶ ካለቀ በኋላ በ4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከ ጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በማ/ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ይከፈታል።
13. አሸናፊ ተጫራቾች ከጽ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም የሚችሉ እና የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በቼክ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
14. አሸናፊው የተገዙ እቃዎችን ለማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ሙሉ በሙሉ በራሱ ወጪ ማቅረብ ይኖርበታል። ወጪ ማቅረብ
15. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
16. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ እና የማይነበቡ ነገር ልኖር አይገባም
17. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ በግልጽ ተለይቶ ሊቀመጥ ይገባል፡፡
18. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፦ 0472260145/ 0472260016 ይደውሉ።


በጅማዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for supplying office, cleaning, printing, food, clothing, construction, electronics, motorcycles, generators, tires, and related items to government offices in Manna District, Jimma Zone, Oromia. Bidders must hold valid licenses, tax clearance, TIN, VAT registration, and meet other stated requirements.
Save Tender