የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የማስተዋወቂያ ቁሳቁሶች ህትመት እና አቅርቦት በግልጽ ጨረታ በማእቀፍ ግዥ አወዳድሮ ለአንድ አመት ውል በመግባት የማስተዋወቂያ እቃ ከነ ህትመት መግዛት ይፈልጋል::
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ግ.ጨ /ኢ.ኢ.ኮ /02/2019
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የማስተዋወቂያ ቁሳቁሶች ህትመት እና አቅርቦት በግልጽ ጨረታ በማእቀፍ ግዥ አወዳድሮ ለአንድ አመት ውል በመግባት የማስተዋወቂያ እቃ ከነ ህትመት መግዛት ይፈልጋል:: በዚሁ መሰረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክርወረቀት የሚያቀርቡ፣ ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንደዚሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና መመዝገባቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዕቃ ከነህትመቱ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ባንኮች በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም በማሰራት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ከኢንሹራንስና ከፋይናንስ ተቋማት የሚቀርቡ ዋስትናዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
|
ተ.ቁጥር |
የምድብ ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ (በኢትዮጵያ ብር) |
|
1 |
የማስተዋወቂያ ቁሳቁሶች ህትመት እና አቅርቦት |
ብር 50,000.00 |
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲዲ ኮፒ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው ነሀሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ነሀሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል::
7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ _ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው፡፡
8. ኮርፖሬሽኑ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
ሕንጻ 1 አራተኛ ፎቅ በኮርፖሬት አገልግሎቶች የግዥ ቡድን ቢሮ የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል (የኢፌዴሪ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ
ኮርፖሬሽን ወይም
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ፌት ለፊት)
ቦሌ ክፍስ ከተማ ወረዳ 05
ስልክ ቁጥር +251 118720722
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን
