Tender Detail

Tender Details


በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ከ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ከ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ግዥ በሎት 1- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ፣ በሎት 2፡- የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃ ግዥ በሎት 3፡- የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፣ በሎት 4፡- የጽህፈት መሳሪያ ግዥ በሎት 5- የደንብ ልብስ ግዥ፣ በሎት 6፡- የሞተር ሳይከል ግዥ በሎት 7 የህትመት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በሚጠይቀው ዘርፍ የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ያላቸው፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  5. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር፣
  6. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው ከገቢዎች መ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ለሎት 1፡- የኤሌክትሮኒከስ ዕቃ ግዥ ብር 50,000 ብር/ሃምሳ ሺህ/ ብር

ለሎት 2- የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃ ግዥ ብር 50,000 ብር/ሃምሳ ሺህ/ ብር

ለሎት 3፡- የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ብር 50,000 ብር/ሃምሳ ሺህ ብር/

ለሎት 4፡- የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ብር 50,000 ብር/ሃምሳ ሺህ ብር/

ለሎት 5፡- የደንብ ልብስ ግዥ ብር 40,000 ብር/አርባ ሺህ ብር/

ለሎት 6፡- የሞተር ሳይክል ግዥ ብር 50,000 ብር/ሃምሳ ሺህ ብር/

በሎት 7፡- የህትመት አገልግሎት ግዥ 40,000 ብር/አርባ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር አፍ ከሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
  3. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471355629

የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣

✨ messages.ai_summary
Open tender by Bench Sheko Zone Finance Department for procuring goods/services across 7 lots: electronics, office furniture, hotel hospitality, stationery, uniforms, motorcycles, and printing services. Bidders must hold valid trade licenses, TIN, VAT registration, supplier certificates, and tax clearance.
Save Tender