ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሂሳብ እንቅስቃሴ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት አወዳድሮ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈለጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር CEDCSE/ NO 05/2018
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሂሳብ እንቅስቃሴ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት አወዳድሮ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ማስደረግ ይፈለጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች :-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ፈቃዳቸውንና ምዝገባ ሰርተፍኬታቸውን ለ2018 ዓ.ም ያሳደሱ፤ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘረውን እያንዳንዱን ዋጋ ሞልተው / ፈርመው እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ፋይናንሻል ኦርጂናል ዶክመንት አንድ እና ፋይናንሻል ኮፒ ሁለት ቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት አንድ እና ቴክኒካል ኮፒ ሁለት ለየብቻ በማድረግ እና በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በቀኑ 8፡30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ቴክኒካል ዶክመንት ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ በነፃ ከድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912818102/0955445261 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የድርጅቱ አድራሻ ሆሳዕና ከተማ ወደ ወልቂጤ መውጫ መንገድ ካቶሊክ ት/ቤት ጎን ላይ ሆሳዕና ኢትዮጵያ
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Central Ethiopia Design and Construction Supervision Enterprise seeks an external auditor for its 2018 budget year financial activities via open national tender. Bidders must have renewed licenses, tax clearance, VAT registration, and submit sealed technical and financial documents.
