የካ/ከ/ከ/ዋ/ስ/አስ/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር አገልግሎት ግዥ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የካ/ከ/ከ/ዋ/ስ/አስ/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2019 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር አገልግሎት ግዥ
- ሎት 1 የአዳራሽ ዲኮር እና የሸራ ድንኳን ኪራይ አገልግሎት ግዥ (CPO -20.000)
- ሎት 2 የወንበርና የጠረጴዛ ጥገና አገልግሎት ግዥ (CPO -5,000)
- ሎት 3 የህትመት ውጤቶች የገልግሎት ግዥ (CPO -20.000)
- ሎት 4 አይሱዙ የጭነት መኪና 35 ኩንታል የሚጭን ኪራይ አገልግሎት ግዥ ከ/ሃገር (CPO=20,000)
- ሎት 5 1ኛ ደረጃ አገር አቋራጭ አውቶቢስ 65 ሰው የሚይዝ ኪራይ አግልግሎት ግዥ h/YIC (CPO -20,000)
- ሎት 6 1ኛ ደረጃ አገር አቋራጭ አውቶቢስ 65 ሰው የሚይዝ ኪራይ አገልግሎት ግዥ አ/አ ውስጥ በሁሉም ከ/ከተማ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ (CPO -20,000)
- ሎት 7 አይሱዙ የጭነት መኪና 35 ኩንታል የሚጭን ኪራይ አገልግሎት ግዥ አ/አ ውስጥ በሁሉም ከ/ከተማ ውስጥ (CPO 20,000)
- ሎት 8 የውሃ፣ ቆሎ እና የተለያዩ መስተንግዶዎች አገልግሎት ግዥ (CPO 10.000)
- ሎት 9 የኮምፒውተር፣ የፐሪንተር፣ ፎቶኮፒ ማሽንና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና መለዋወጫ አገልግሎት ግዥ (CPO -10,000)
- ሎት 10 የአቃቤ ህጎች የፕሮቶኮል ልብስ ግዥ (CPO -50,000)
- ሎት 11 የደንብ ልብስ (CPO 10,000)
- ሎት 12 የጽዳት እቃዎች ግዥ (CPO -5,000)
- ሎት 13 የእንስሳት መድሃኒት ግዥ (CPO -20,000)
- ሎት 14 አሉሚኒየም ድንኳን ኪራይ አገልግሎት ግዥ (CPO =20,000)
ስለዚህ በጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ተጋብዘዋል፡፡
- የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና እንዲቀርብ የተጠየቁባቸውን እቃዎች መጫረቻ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የተጠየቀውን ወይም የሚወዳደሩበትን ናሙና ማስገባት ግዴታ ነው፡፡
- የዘመኑ ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከሪያ ሲፒኦ ከላይ በተገለፀው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ የየካ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ አርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒ መሆኑን በመግለፅ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙ በመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ውስጥ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆኑን አለመሆኑን ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ የውል ማስከበሪያ CPO 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ሎት 13 የእንስሳት መድሃኒት ቫት ማቅረብ አይገደዱም፡፡
የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
ስልክ ቁጥር:- 011-8-67-81-75
የካ/ክ/ከ/ዋ/ስ/አስ/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
✨ messages.ai_summary
Open tender for 14 service procurement lots, including hall decor, tent rental, furniture repair, printing, truck/bus rental, hospitality, IT equipment repair, uniforms, cleaning supplies, animal medicine, and more. Bidders must hold valid trade licenses, tax registration, and required certifications.
