በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ማናቸውም ህጋዊ እውቅና ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን አረርቲ ከተማ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የምትጫረቱበትን ዋጋ ሰነዱን በመግዛት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እንድታቀርቡ እያሳሰብን ጨረታው በአየርላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 /አራት ሰዓት ተኩል/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታው ሲቀርቡ ማሟላት የሚጠበቅባቸው ሰነዶች:-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ
- የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት
- የግብር ከፋይነት ምስከር ወረቀት
- ለተጨማሪ ታክስ ግብር ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ ማስረጃ
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒ/ ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው። መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ/0222230144 ሞባይል 0922659065
የአረርቲ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
✨ messages.ai_summary
The Arerti Town Water and Sewerage Service Office seeks bids for the procurement of pipes and pipe fittings. Eligible bidders must have a valid business license, registration, and tax clearance. Bids must be submitted in sealed envelopes with required documentation.
