በአዲስ አበባ የምርታማት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የእቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ የምርታማት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም
የጨረታው የመወዳደሪያ መስፈርት
- ሎት 1. ኮንስትራክሽን እቃዎች
- ሎት 2 የኮምፒውተር/አይሲቲ እቃዎች
- ሎት 3. የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች
- ሎት 4. የማኑፋክቸሪንግ እቃዎች
- ሎት 5. የሌዘር ቴከኖሎጂ ዕቃዎች
- ሎት 6. የእንጨት ስራ እቃዎች
- ሎት 7. የአውቶሞቲቭ እቃዎች
- ሎት 8. የጋርመንት እቃዎች
- ሎት 9. የደንብ ልብስ
- ሎት 10. የህትመት ዕቃዎች
- ሎት 11. የስቴሽነሪ ዕቃዎች
- ሎት 12. የከሊኒክ ሕክምና ዕቃዎች
- ሎት 13. የተለየዩ ማሽኖች ጥገና
- ሎት 14. የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 15. የፕለይ ግረወንድ ዕቃዎች
- ሎት 16. የስፖርት ትጥቅ
ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ዌብሳይት ላይ በአቅራቢዎች ሊስት ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ በCPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
የጨረታ ዋስትና
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ያለባቸዉ የዋጋ ዝርዝር
| ሎት 1 | ብር 80,000.00 |
| ሎት 2 | ብር 50,000.00 |
| ሎት 3 | ብር 100,000.00 |
| ሎት 4 | ብር 70,000.00 |
| ሎት 5 | ብር 50,000.00 |
| ሎት 6 | ብር 150,000.00 |
| ሎት 7 | ብር 150,000.00 |
| ሎት 8 | ብር 50,000.00 |
| ሎት 9 | ብር 20,000.00 |
| ሎት 10 | ብር 20,000.00 |
| ሎት 11 | ብር 30,000.00 |
| ሎት 12 | ብር 40,000.00 |
| ሎት 13 | ብር 40,000.00 |
| ሎት 14 | ብር 20,000.00 |
| ሎት 15 | ብር 40,000.00 |
| ሎት 16 | ብር 40,000,00 |
ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና መለያ ቁጥር/ቲን ነበር ያላቸው መሆን አለባቸው
ተጫራቾች አሸናፊ ያሸነፉበትን 10% በCPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት ብር 250.00(ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመከፈል ልደታ ጤና ጣቢያ አጠገብ በሚገኘው የምርታማነት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል 3ኛ ፎቅ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል ኦርጅናልና ቴከኒካል ኦርጅናል፣ ፋይናንሻል ኮፒና ቴከኒካል ኮፒ ኢንቨሎፕ በ4 ፖስታ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ የማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ፖስታ ተቀባይነት የለውም የቀረበው ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ያለበት በሁሉም ሎቶች ስሆን ከባድ የሆነ ዕቃ በፎቶ እና ካታሎግ ማቅረብ አለበቸዉ ::
የጨረታ ሰነዱ የዋጋ መሙያ ውጪ ተሞልቶ የሚመጣ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠትም ሆነ ጨረታው ማስገባት ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
ጥቃቅንና አነስተኛ የሆናችሁ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃችሁ ከ/ከተማ በአድራሻችን የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ማሽን ነከ ነገርላይ ሲፒኦ ማስያዝ አለበቸዉ፡፡
ማዕከሉ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ልደታ ጤና ጣቢያ ጀርባ ወይም በአፍሪካ ህብረት አደባባይ ወደ ልደታ ጸበል በሚወስደው መንገድ የምርታማነት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል 3ኛ ፎቅ ስበስm መረጃ
ስልክ ቁጥር 011-51-57-635
በአዲስ አበባ ከተማ የምርታማነት ማሻሻያና የልህቀት ማዕከል
