ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን የፅዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ሰሜ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/011/2018
ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን የፅዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
| የዕቃዉ አይነት | የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የመከፈቻ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ ዋስትና መስከበሪያ |
| የፅዳት እቃዎች | ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት | እሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም 4:30 ሰዓት | 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨ.እ.ታ፤ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 400,00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000149984384(EEU N/A/A/R CU CON FOR EL CON) በሚለው ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- ፒያሳ አቡጎጴጥሮስ ፊት ለፊት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-210 በሚገኘው ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ግዥ እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸፈ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ «ኦሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ሰሜ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/011/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0984820007 መደወል ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን
✨ messages.ai_summary
North Addis Ababa Region seeks bids from qualified cleaning supply companies for the open procurement of cleaning items. Eligible bidders must hold a renewed trade license, VAT registration, tax ID, and proof of registration on the procurement agency website.
