በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የደቡብ ኦሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በፑል ለሚተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በማወዳደር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎት መሰረት፦
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የደቡብ ኦሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በፑል ለሚተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በማወዳደር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎት መሰረት
ሎት 1. የጽ/መሳሪያ እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች
ሎት 3. የሰራተኞች ደንብ ልብስ
ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ሎት 5 የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ፈርኒቸር
ሎት 6. ሞተር ሳይክል
ሎት 7. የሕትመት ሥራዎች
ሎት 8. እሽግ ውሃዎች
ሎት 9. የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
ሎት 10. የተሽከርካሪዎች ዘይትና ቅባት
በሀገር አቀፍ ደረጃ በግልጽ ጨረታ ግዥ ዜዴ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታውለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
1. በሁሉም መስኮች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም ፍቃድ ያሳደሱ።
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (tin number) እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት (VAT) ማስረጃ እንዲሁም ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የንግድ የምዝገባ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO በሚያስገቡበት የጽ/መሳሪያ እና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ብር 25,000.00/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ እና ለጽዳት ዕቃዎች ብር 15,000/አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሰራተኛ ደንብ ልብስ 25,000/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 35,000.00/ሰላሳ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ ለሞተር ሳይክል 35,000.00/ሰላሳ አምስት ሺህ ብር/፣ ለፈርኒቸር 25,000.00/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ለሕትመት ሥራዎች 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ለእሽግ ውሃዎች 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ለሞተር ሳይክልና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር ብቻ/ የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት 25,000.00/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በህግ ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ በእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከደቡብ ኦሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ከግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 ቀርቦ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሰነድ በ16ኛው አስራ ስድስተኛው የሥራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡30 ሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
7. የጽ/መሳሪያ እና ሎሌች አላቂ ዕቃዎች ፣ ጽዳት ዕቃዎች ፣ የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ፈርኒቸር፣ ሞተር ሳይክል እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ሲሆን የሕትመት ስራዎች እሽግ ውሃዎች፤ መኪና እና ሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት በ17ኛው ቀን የሥራ ቀን ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
8. ጨረታው በዚያው ቀን 8፡30 ሰዓት ባለቤቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው ሲከፈት የተጫራቾች ያለመሟላት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም። ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ኦርጅናል ዶክመንቶቻቸውን ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር +251 91 351-0135 ወይም +251 97 277-5960
የደቡብ ኦሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
ዲመካ
