Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ /ኢ/ክ/መንግሥት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address በማዕከላዊ /ኢ/ክ/መንግሥት፣ኢትዮጲያ, Phone: 011-330-0112
  • Website
  • Deadline04 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 100/አንድ መቶ ብር
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ 11 ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Electrical And Electromechanical , Ict Equipment'S And Its Accessories , Equipment And Accessories

በማዕከላዊ /ኢ/ከ/መንግስት የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የማህበረሰብ ቴሌቪዢን ለማስጀመር የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ እቃዎች ግዢን ለመፈጸም ተጫራቾችን ለማወዳደር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018-2019

በማዕከላዊ /ኢ/ከ/መንግስት የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የማህበረሰብ ቴሌቪዢን ለማስጀመር የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ እቃዎች ግዢን ለመፈጸም ተጫራቾችን ለማወዳደር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው
  4. የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  5. የግዢው መጠን ከብር 500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፤ የአምራቹን ስም ፤ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጋር መያያዝ አለበት ፤
  8. ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለባቸው፣
  9. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤
  10. ተጫራቾች የተገለፀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር በጉ/ዞ/ገ/መምሪያ በመከፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፣
  11. ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር/10/ተከታታይ ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው ፤
  12. ጨረታው በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚህ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ፋይናንስና መምሪያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፤
  13. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  14. ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-330-0112 ደውለው መጠየቅ ይቻላል
  15. የመከፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን የሚሸጋገር መሆኑ እንገልጻለን

ማሳሰቢያ ፦ ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ ተጫራቾች 90 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡

በማዕከላዊ /ኢ/ክ/መንግሥት የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Open tender for the purchase of electronic equipment to launch a community television by the Gurage Zone Government Communication Affairs Department. Bidders must have a valid trade license, tax clearance, TIN, and supplier registration certificate.
Save Tender