በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት በክ/ከተማ አስተዳደር ለሚገኙት መንግስት መ/ቤቶችና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ በሎት፡-
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት በክ/ከተማ አስተዳደር ለሚገኙት መንግስት መ/ቤቶችና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ በሎት፡-
የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የንጽህና መሳሪያዎችን፣ ቋሚ-አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፣ የሠራተኛ የደንብ ልብሶችን፣ የተለያዩ ቀለሞችን፣ በሎት 2፡- የኤሌክትሮኒክስ፤ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችንና የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ በዘርፉ ህጋዊ ታደሰ የንግድ ፍቃዱ ያለውና በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟለው የንግድ ድርጅት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 1,000 ብር (አንድ ሽህ ብር ብቻ) ወደ ሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1064669901216 ገቢ በማድረግ (በመከፈል) ደረሰኙን በመያዝ ከፉሪ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል::
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመከፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ ከባንክ የተረጋገጠ CPO 150,000.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ሽህ ብር ብቻ) በፉሪ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከሰነድ ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል (የሲንቄ ባንክ CPO ቢሆን ይመረጣል)::
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ስምና አድራሻ በማድረግ በድርጅቱ ስልጣን ባለው አካል ማህተምና ፊርማ በማረጋገጥ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በፉሪ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት አለበት ::
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል:: እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ከስቶክ ወይም ከራሳቸው ስቶር ሆኖ እቃዎቹ ጥራቱን የጠበቁ መሆን ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ሊያቀርቡት ዋጋ ያሉትን 1 እቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው ሰነድ በማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን፣ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል:: እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል::
- ግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ፉሪ ይገኛል:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910489372፤ 0938173674 ደውለው መጠየቅ ይቻላል::
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
