ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ከዚህ በታች በተለያየ ጥቅል የተገለፁትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
| ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ Nile Insurance Co. S.C
ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ከዚህ በታች በተለያየ ጥቅል የተገለፁትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡– 1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ብቁ ልምድ ያላቸው፡፡ 2. ተጫራቾች ስለ ጨረታው የሚገልፀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ከነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋናው መ/ቤት ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ (22ኛ ፎቅ) በመምጣት ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ 3. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ ጥቅል ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚጫረቱበት ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የመጫረቻ ሰነድ እና ዋጋ በኤንቬሎፕ በማሸግ እስከ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የኩባንያው ዋና መ/ቤት 22ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 5. ጨረታው በዕለቱ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 6. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት (ብሔራዊ ቴአትር ጀርባ) ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ (22ኛ ፎቅ) የስልክ ቁጥር፡- 0911480845/0911430292 አዲስ አበባ፡፡ |
