Tender Detail

Tender Details

  • Company የመቂ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Address ምሥራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0912999499
  • Website
  • Deadline12 Sep 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing

የመቂ ከተማ ውሃ ና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ 2019 በጀት ዓመት የአዳራሽ ወንበር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የመቂ ከተማ ውሃ ና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ 2019 በጀት ዓመት የአዳራሽ ወንበር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፋ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም መሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት አሟልቶ ላልቀረበና ማንኛውንም ስህተት ቢፈፅም ኃላፊነቱ የተጫራቹ/ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል፡፡
  6. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልፅ መፃፍ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም የመቂ ከተማ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ መሞላት አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ) የCPO ቼክ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ ያቀረበው ዋጋ ለሶስት (3) ወር ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን የዋጋ ለውጥ የሚካሄደው ከሶስት ወር በኃላ በገበያ ጥናት አሸናፊው ድርጅት በሚያቀርበው ዋጋ ተንተርሶ በሚሰጥ ዋጋ ይሆናል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት ውል በገባ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዕቃውን በድርጅቱ መስሪያ ቤት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ አርጅናል መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰንዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ቴክኒክና ፋይናስ በተናጠል በታሸገ ኢንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈው ከጠቅላላ ዋጋ 10/100 ለድርጅቱ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራች በአካል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  16. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2001 እና FA 1/2009 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 157/2002 መሠረት ጽ/ቤቱ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡
  17. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ-

የሚፈለገው የወንበር ብዛት የምናሳወቀው የማሻነፊያ(የጨረታ) ዋጋ ከተለየ በኃላ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋ ከቫት ጋር መሆኑን እና ያለመሆኑን የጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ መፃፍ ይኖርበታል፡፡

ለበለጠ መረጃ በሞባይል ቁጥር 0912999499 ወይም 0913197403 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡- ምሥራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ የመቂ ከተማ ውሃ ና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

የመቂ ከተማ ውሃ ና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Meki Town Water and Sewerage Service Enterprise seeks bids for the open tender procurement of hall chairs for the 2019 budget year. Bidders must hold a renewed trade license, tax clearance, VAT registration, TIN, and supplier certificate. Items must be original, with samples required.
Save Tender