Tender Detail

Tender Details


ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የመስቀል አደባባይ ፋሲሊቲ ማኔጅመንት የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ)፣ ደህንነት ለመጠበቅና ድገተኛ የእሳት አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎችን፣ የሙሌት ጥገና አገልግሎት (Fire Extinguishers, Refill/Maintenance Services) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


1.  የጨረታ ማስታወቂያ (Invitation for Bids)

ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት የመስቀል አደባባይ ፋሲሊቲ ማኔጅመንት የመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ)፣ ደህንነት ለመጠበቅና ድገተኛ የእሳት አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎችን፣ የሙሌት ጥገና አገልግሎት (Fire Extinguishers, Refill/Maintenance Services) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡-

  • በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከታክስ ባለስልጣን የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችሉ፤

2.  የተጫራቾች መመሪያ (Instructions to Bidders)

  • የጨረታ ሰነድ ስለመግዛት፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መስቀል አደባባይ በሚገኘው ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ፋይናንስ መምሪያ የማይመለስ ብር 00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5,000.00 አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በ “Exhibition Center & Market Development Enterprise” ስም አዘጋጅተው ከቴክኒክ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

•  የሰነድ አሸሻግና አቀራረብ፡

  • ተጫራቾች የቴክኒክና የፋይናንስ መወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ “ኦሪጅናል” እና “ኮፒ” በማለት በግልጽ ጽፈው ሁለቱን በአንድ ላይ በማድረግ ትልቅ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ CPO ከቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  • ሁሉም ፖስታዎች በሰም የተሸጉ፣ የተጫራቹ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያረፈባቸው መሆን አለባቸው፡፡
  • የጨረታ ሳጥን መዝጊያና መክፈቻ፡ ጨረታው መስከረም 06 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  • የዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ፡ የቀረበው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 (ዘጠና) ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  • የውል ማስከበሪያ (Performance Security) አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የሰራ ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ውል ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡

ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ዘግይተው የሚደርሱ የጨረታ ሰነዶች ሳይከፈቱ ለተጫራቹ ይመለሳሉ፡፡

Save Tender