የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ ኃይል ለረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃ/ማ/ጣቢያ የጥበቃ እና የጽዳት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EΕΡ/GBP/NCB/11/2018
የኢትዮጵያ ኤሌከትሪክ ኃይል ለረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኃ/ማ/ጣቢያ የጥበቃ እና የጽዳት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ
በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
-ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት መሳሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ህንጻ 1ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሕዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ጀነሬሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ቁጥር 114 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የጥበቃ እና የጽዳት አገልግሎት ግዥ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/GBP/NCB/11/2018 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦርጅናል እና 2(ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ለሎት-1 ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) እና ለሎት2 ብር 15.000.00 (አስራ አምስት ሺህ) ለ60 (ስልሳ) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይየባንከ ከፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም ተዘጋጅቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ጨረታው ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00ሰአት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰአት ሕዳሴ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ጀነሬሽን ቢዝነስ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-ተጫራቶች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 011-5 57 40 12 መደወል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
