በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለባሶ ሊበን ወረዳ እንስሳት ሃብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት በተዘዋዋሪ ፈንድ በጀት የእንስሳት መድሀኒት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለባሶ ሊበን ወረዳ እንስሳት ሃብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት በተዘዋዋሪ ፈንድ በጀት የእንስሳት መድሀኒት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች
1. ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ፍቃዳቸውን ያሳደሱ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ
3. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1- 2 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 8500/ ስምንት ሺህ አምስት መቶ/ ብር በመሂ-1 ወይም በCPO ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት የማይመለስ 50 ብር ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ይህ ግልፅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀን በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በእዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 3 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎች ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመከፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡
7. ውድድሩ በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ አሸናፊ የሚለይ በመሆኑ ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ የሁሉንም ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን የሚገልፅ የድርጅቱን ማህተም ፣ስም እና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
8. በጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 10% የውል ማስከበሪያ በማቅረብ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን በተገለጸው የጊዜ ገደብ ውስጥ 10% ውል ካልያዘ /ካልፈረመ/ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ መ/ቤቱ ውርስ ያደርጋል፡፡
9. አሸናፊው የአሸነፈበትን ትክክለኛ መድሃኒት ባሶ ሊበን ወረዳ እንስሳት ጽ/ቤት ንብረት ከፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
10. ተጫራቾች ዋጋ መሙያው ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለባቸውም፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
11. የባ/ሊ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በጫራታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 246 0316/0565 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
