ለዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የባለሙያ ልብስ እና የአስተዳደር ሰራተኞች የልብስ ስፌት የአገልግሎት ግዢ፣የስራ መገልገያና የደንብ ልብስ ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2017
ለዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ ከታች በተገለፁት ሎቶች መሰረት፡-
- በሎት 1፡- የባለሙያ ልብስ እና የአስተዳደር ሰራተኞች የልብስ ስፌት የአገልግሎት ግዢ
- በሎት 2፡- የስራ መገልገያና የደንብ ልብስ ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን የተጫራቾች መመሪያ ማክበር አለባቸው:-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በዝ፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ እና ከገቢዎች የታደሰ የመጫረቻ ፈቃድ ደብዳቤ የሚያቀርቡ ሆኖ ሁሉንም ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው። የተጠየቁ ማስረጃዎች በግልፅ የሚታይና የሚነበብ ፎቶ ኮፒ በማደረግ ማቅርበ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ በማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅዳሜ ዕሁድና የበዓል ቀናትን ሳይጨምር በሚቆጠር እስከ 10ኛው ቀን 10፡45 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሆስፒታሉ የፋይናንስ ዳይሬከቶሬት ከፍል ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ፖስታዎቹ ላይ ከውጪ ሎቶቹን በመፃፍና ማህተም በማድረግ፣በየሎቱ ለየብቻ ተለይተው ኦሪጂናልና የማይመለስ ኮፒውን በመለየት የሚቀርቡ ሆኖ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ወይም እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ግዢ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ቡድኑ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ በ ሎት-2 ላይ ሳምፕል ያቀርባሉ
- በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ (በዚሁ ዕለት) በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ቡድኑ ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና፦ ሎት-1 ብር 5000.00 (አምስት ሺ)ብር፣ ሎት-2 ብር 10000.00 (አስር ሺ )ብር፣ በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) በሆስፒታሉ ስም የተዘጋጀ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ በተቀመጠው ሰነድ መሰረት ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ በመለየት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሀሳብ ካላቸው ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሆስፒታሉ የግዥና ዕቅድ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት የስራ ከፍል በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊዎች ተለይተው ውል አስኪፈጸም ድረስ እንደተያዘ ይቆያል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባለው የቅሬታ ማቅረቢያ የሚታይበትን ቀን ጨምሮ ከ7 ቀን በኋላ አሸናፊዎች አዋርድ ወስደው 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ በማስያዝ በሶስት ቀን ውስጥ ውል ተዋውለው በጨረታ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በስፔስፊኬሽኑና እና ሳምፕል የቀረበባቸውን በሳምፕሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጫረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል።
- የጨረታውን 20% መጨመርና 20% መቀነስ ይቻላል።
- ሆስፒታሉ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-515-02- 42 በመደወል መረዳት ይቻላል።
- አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፍል ውሀ ፊት ለፊት ይገኛል
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል
