በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ2017 በጀት አመት ከመደበኛ እና ካፒታል በጀት ለመ/ቤቱ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ማሸነሪዎች አገልግሎት የሚውል መለዋወጫ (ስፔር ፓርት) በሎት 1/አንድ/ እንዲሁም ጎማና ባትሪ በሎት 2/ሁለት/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በ2017 በጀት አመት ከመደበኛ እና ካፒታል በጀት ለመ/ቤቱ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችና ማሸነሪዎች አገልግሎት የሚውል መለዋወጫ (ስፔር ፓርት) በሎት 1/አንድ/ እንዲሁም ጎማና ባትሪ በሎት 2/ሁለት/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸዉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ብር የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በማስላት በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው የዋጋ አሞላል ብቻ መሙላት አለበት:: በሚጠይቀው ዋጋ አሞላል ካልሞሉ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል።
- የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት /በጥቅል/ ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዝረዝር መግለጫ (ስፔስፊኪሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ20/02/2017 ዓ/ም እስከ 4/3/2017 ዓ/ም 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖሰታ መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በግዥና/ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 5/3/2017 ዓ/ም ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥና ፋይ/ን/ አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በ 5/3/2017 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻልን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 351 33 37/033 551 05 04/ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- የመስሪያ ቤቱ አድራሻ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ህንጻ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 ላይ ነው፡፡
አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር
መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት
