በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በስሩ ለሚገኙ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሰው መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/ 2017
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በስሩ ለሚገኙ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሰው መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በዘርፉ አግባብ ያለውና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ የተጨማሪ እሴት ታከስ/ቫት/ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የታክስ ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ተያያዥ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለተራ ቁጥር 1 ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በኢትዮጵያ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት የብር 25.000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) CPO በድርጅቱ ትክከለኛ ስም ላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢንተርፕራይዙ አስ/ፋይ/አገ ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈርመው ወኪል ከሆነ ከሚመለከተው ውክልና ሰጪ (መዝጋቢ እካል) የተሰጠ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት ዋናና አንድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ የተጫራቹ ድርጅት ማህተም ተደርጎበትና ተፈርሞ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ብሎክ 20 ቢሮ ቁጥር 2023 በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ አስ/ፋይ/አገ/ ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው ቀን እና ቢሮ ከጠዋቱ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፤ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ባይገኙም ሰነዳቸው የተሟላ ሆኖ ከተገኘ በሌለበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የመወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም። ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን ዕቃ የኢንተርፕራይዙ ንብረት ከፍል የሚገኝበት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ላሸንፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በኢትዮጵያ በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት CPO ውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራች በውሉ ውስጥ የተካተቱትን ህጐች ማከበር አለባቸው፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 0914711156 መጠቀም ይችላል።
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና ማማከር
ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
