Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Police College (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ)
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0942410695
  • Websitehttps://oromiapolicecollege.edu.et
  • Deadline05 Dec 2024, 12:30 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Textile, Garment & Leather

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓ.ም ለሰልጣኞች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቢሮ እቃዎች፤ የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የውሃ ዕቃዎች የመብራት ዕቃዎች፤ የተለያዩ የግንባታ ጥገና እቃዎች፣ የቢሮ የቢሮ እና የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮች እና የተለያዩ አይነት አልባሳትን ማለትም የእስፓርት ልብስ ቱታ ቶርሽን ጫማ፤ ቁምጣ እና ቲሸርት፤ የጀርባ ቦርሳ፤ ትልቁ ፎጣ የሻወር፤ መካከለኛ ፎጣ የራስ የእስፖርት ኮፊያ፤ ፊሽካ ለቶርሽን ጫማ የሚሆን ካልሲ እና ጥቁር ካልሲ ወፍራም ለከስክስ ፎጣ የሚሆን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የግዥ  ግልፅ  የጨረታ  ማስታወቂያ  2/2017

የጨረታ  ቁጥር  ኦፖኮ/02/2017

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ 2017 የበጀት . ለሰልጣኞች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቢሮ እቃዎች፤ የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የውሃ ዕቃዎች የመብራት ዕቃዎች፤ የተለያዩ የግንባታ ጥገና እቃዎች፣ የቢሮ የቢሮ እና የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮች እና የተለያዩ አይነት አልባሳትን ማለትም የእስፓርት ልብስ ቱታ ቶርሽን ጫማ፤ ቁምጣ እና ቲሸርት፤ የጀርባ ቦርሳ፤ ትልቁ ፎጣ የሻወር፤ መካከለኛ ፎጣ የራስ የእስፖርት ኮፊያ፤ ፊሽካ ለቶርሽን ጫማ የሚሆን ካልሲ እና ጥቁር ካልሲ ወፍራም ለከስክስ ፎጣ የሚሆን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ አዳማ የጨረታውን ሰነድ በመግዛት ጨረታው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለመወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች፤ ነጋዴዎች አቅራቢዎች ፤-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ 2016/2017 ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  2. የሥራ ግብር ከፋይ መሆኑን የሚገልፅ የቲን ቁጥር መረጃ ማቅረብ የሚችል
  3. ተጫራቾእ በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር (Supply List) ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
  4. ግብር መከፈላቸውን የሚገልፅ መረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችል፣
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT 15%) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
  6. ማንኛውም ተጫራች ለውድድር ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ (CPO) 2% ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
  7. የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በኦሮሚኛ ቋንቋ ስለሆነ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበትን ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ የጨረታ ሰነዱን በኮሌጅ ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በማቅረብ መውሰድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጥል በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው::
  9. የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሁድን ሳይጨምር 15 (አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ 16ኛው ቀን እስከ 600 ሰዓት ተሸጦ የጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 630 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከሰዓት በኋላ 800 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ በኮሌጁ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  10. ኮሌጁ በሚገዛው ማንኛውም ዕቃ ላይ 50% የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር 0942410695 0913379464 አና 0941734430 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

 

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ

Save Tender