Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Engineering Corporation (የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን)
  • Address ከመገናኛ አደባባይ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚወስደው ዋና ቀለበት መንገድ ወደ አደይ አበባ ስታዲዬም (የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ማእከል) የሚያስገባው መገንጠያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጥበት ህንጻ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 118720722
  • Websitehttps://eec.com.et/
  • Deadline10 Dec 2024, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Health Care, Medical Industry

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በቀድሞው ስሙ የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተብሎ ሲጠራ የነበረው በስሩ ለሚገኙ ከ3,000 በላይ ሠራተኞች የተሟላ የአጠቃላይና የልዩ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ብቃት ያላቸው ሆስፒታሎች ወይም የህክምና ተቋማት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

    የጨረታ  መለያ  ቁጥር  ግጨ/../07/2017

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በቀድሞው ስሙ የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ተብሎ ሲጠራ የነበረው በስሩ ለሚገኙ 3,000 በላይ ሠራተኞች የተሟላ የአጠቃላይና የልዩ ህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ብቃት ያላቸው ሆስፒታሎች ወይም የህክምና ተቋማት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል። በዚሁ መሰረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋማት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የጤና ተቋማቶችና ምርመራ ማዕከል የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የህክምና አገልግሎት የሚሰጡበት በቂና በዘመናዊ መሣሪያ የተደራጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወደም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም በማሰራት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፦

ምድብ

የምድብ ዝርዝር

 

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ (በኢትዮጵያ ብር)

1

ለአጠቃላይ ህክምና

          ብር 40,000.00

2

የዓይን ህክምና

          ብር 10,000.00

3

የጥርስ ህክምና

          ብር 10,000.00

4

የማህፀንና ጽንስ ህክምና

          ብር 10,000.00

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ጨረታው ታህሳስ 01 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ታህሳስ of ቀን 2017 ከጠዋቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል።
  3. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ የውል ማስከበሪያ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ለሎት አንድ ብር 50,000.00 እንዲሁም ለሌሎቹ ምድቦች ብር 20,000.00 በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና ድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው።
  5. ኮርፖሬሽኑ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡-

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /በቀድሞ ስሙ የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን

ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን/

ሕንጻ 1 አራተኛ ፎቅ በኮርፖሬት አገልግሎቶች የግዥ ቡድን ቢሮ

ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ ህንፃ

(የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል) ፊት ለፊት

ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05

ስልክ ቁጥር ፡- +251 118720722

 

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

Save Tender