ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) ማለትም ሙሉ ልብስ ኮትና ሱሪ፤ ሸሚዝ፣ ጫማ፡ ጋወን፤ የሴፍቲ ቱታ፡ የሴፍቲ ጫማ፣ ኖርማል ቱታ እና ሽፎን ጨርቅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) ማለትም ሙሉ ልብስ ኮትና ሱሪ፤ ሸሚዝ፣ ጫማ፡ ጋወን፤ የሴፍቲ ቱታ፡ የሴፍቲ ጫማ፣ ኖርማል ቱታ እና ሽፎን ጨርቅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ፡-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከፋይናንስ ከፍል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት መመዝገቢያ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀው የብር መጠን በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራች የእያንዳንዱ እቃዎች ብራንዳቸውንና ሌሎች የዕቃው መገለጫዎች በጨረታ ሰነዱ መሰረት መገለጽ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር በመረጡት በእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በድርጅቱ ማቅረብ ይኖርበታል።
- በጨረታ የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልፅና በማያሻማ መልኩ መፃፍ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት በይሓ ሪል እስቴት ንብረት ከፍል 11ኛ ፎቅ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 8 /ስምንት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከድርጅቱ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8 /ስምንተኛው የሥራ ቀን/ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 8 /በስምንተኛው የሥራ ቀን/ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት እና መሳተፍ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር:- የቢሮ 0115580129/12/03 ሞባይል- 0922079575/ 0911417904 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
አድራሻ :- አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት “ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ መምሪያ
ማሳሰቢያ :- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ይሓ ሪል አስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
