የሲዳማ ብሔ/ክል/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በብሔራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔ/ክል/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በብሔራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ኮሚሽኑ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልጋቸው ቋሚና አላቂ ዕቃዎች ዝርዝር:-
❖ የተለያዩ የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች፤
❖ የተለያዩ የቢሮ የፅዳት አላቂ ዕቃዎች፤
- በሚወዳደሩበት መስክ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸውና ያሳደሱ፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ፤ ከመንግስት ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸውና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠየቀውን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታ ከሚያቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እንደፍላጎታቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1.2% የያዘ ሲፒኦ /CPO/ በባንክ የተረጋገጠ ቼከ፤ እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ በማያያዝ ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ከሞሉ በኃላ የጨረታውን ሠነድ አንድ ኦሪጂናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው እንደገና በአንድ ትልቅ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው በኤንቨሎፕ ላይ የተጫራቾች ድርጅት ማህተም አርፎበት በሰም ታሽጎ ፖስታው እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ወደ ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኃላ በዕለቱ ከረፋዱ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በኮሚሸኑ ግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ዕለት ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት /15/ ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታውን ሰነድ በኢትዮጵያ ብር /100/ አንድ መቶ ብር በመክፈል ከግዥና ንብረት አስ/ር ስራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚቀርበው የዕቃ ብዛት በሚሸጠው በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መመሪያውን በሚገባ በማንበብ መወዳደር ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር ማብራሪያ የያዘ ስለሆነ ይበልጥ ተቀባይነት አለው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነታቸው ከተገለፀ ጊዜ ጀምሮ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡ ውል የማይገቡ ከሆን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረስባቸዋል፡፡
- ኮሚሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 046-2-12-78-75 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
