በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት (የፅህፈት መሳሪያዎች (ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች/፤ ሎት 2.የመኪና ጎማ፣ ሎት 3. የመኪና እና የጄነሬተር ሞተር ዘይት፣ ሎት 4. ህትመት፣ ሎት 5.የፅዳት እቃዎች ግዥ እና ሎት 6.የውሃ ጋንፕ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት (የፅህፈት መሳሪያዎች (ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች/፤ ሎት 2.የመኪና ጎማ፣ ሎት 3. የመኪና እና የጄነሬተር ሞተር ዘይት፣ ሎት 4. ህትመት፣ ሎት 5.የፅዳት እቃዎች ግዥ እና ሎት 6.የውሃ ጋንፕ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የሚሞሎት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የሚያቀርቡት እቃ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተጣለባቸው ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ/ፋይ/ ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 62 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ያክሉን ለሆስፒታሉ በCPO /በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- ከብር 10,000.00/አስር ሽህ ብር/ የእቃ ግዥ እና ከብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ በላይ ለሚገዙ የአገልግሎት ግዥ ክፍያ ላይ 2% የመቁረጥ ግዴታ አለብዎት፡፡
- መስሪያ ቤቱ አሸናፊውን ድርጅት የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበውን ድርጅት ሆኖ በሎት 1 ለተቀመጡት ጨረታዎች ለመወዳደር የፅህፈት መሳሪያዎች እና ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች ንግድ ፍቃድ በየዘርፉ /ለየብቻው⁄ ወይም ሁለቱንም የሚገልፅ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለሁሉም ጨረታዎች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- አሸናፈ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ከ5 /አምስት/ ቀናት በኋላ ባሉት 5/ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በCPO / በጥሬ ገንዘብ/ ለሆስፒታሉ በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ ዝርዝር አባሪ ዶክሜንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ በሆስፒታሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ለሁሉም ጨረታዎች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋ መሙያ ላይ ማየት ይቻላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ /ዝግ/ ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀናት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913869679፣ 0924854239 ወይም 0925402088 ደውለው ይጠይቁ፡፡
አድራሻ ፡-
ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ 197 ኪሎ ሜትር ደብረሲና ከተማ ደ/ሲና
የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
