በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/አ//ከ/አስ/ደ/ማ/ባ//ግ/ጨ/03/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው የእቃ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን |
ምርመራ |
|
1 |
አልባሳት |
15,000.00 |
ናሙና የሚቀርብ |
|
2 |
የጽዳት እቃዎች |
3,000.00 |
ናሙና የሚቀርብ |
|
3 |
የፅህፈት መሳሪያዎች እና የኮፒ ፕሪንተር ቀለም |
7,000.00 |
ናሙና የሚቀርብ |
|
4 |
ህትመት |
2,000.00 |
ናሙና የሚቀርብ |
|
5 |
የአሉሚኒም በር ተንጠልጣይ ቁልፍ እና ጥገና አገልገሎት |
2,000.00 |
|
|
6 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
10,000.00 |
ሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ |
|
7 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
20,000.00 |
|
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ ፡-
የሚፈልጉ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን /TIN) ማቅረብ የሚችሉ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናሻል ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻው በማቅረብ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በመንግስት ግዥና ንብረት አ/ጠ/አ/ዳይሬክቶሬት 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09/15 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው ዋጋ ማቅረቢያ ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም። ናሙና የተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት እያንዳንዱ እቃ ጥራት በቴክኒክ ብቃታቸው ከተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- አ/አ አራዳ ክፍል ከተማ (ፒያሳ) ልዩ ስሙ እሪ በከንቱ ተብሎ
በሚጠራው የኢትዮጵያ ስታቲስቲካል አገልግሎት ቢሮ አካባቢ እስጢፋኖስ
መካሻ አማረ (EMA ) ህንፃ 9ኛ ፎቅ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክቁጥር 011 562 2343 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን
