Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ባህር ዳር
  • Address ባህር ዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0582221100
  • Website
  • Deadline19 Feb 2025, 2:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Vehicle tire

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ለማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያላቸውን ጎማ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ለማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያላቸውን ጎማ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / ያላቸው፣
  3. የገዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  5. የሚገዛው የማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያለው ጎማ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/Specification/ ከጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
  6. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል ከገንዘብ ያዥ ከቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን 27/05/2017 . ጀምሮ እስከ ቀን 12/06/2017 . ማግኘት ይቻላል፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (../ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፤ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ ማስገባት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy)በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት‍‍‌‍‍‍‌‍‍‍‍‌‍‌‍ ይህ ማስታወቂያ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት ቀን 27/05/2017 / ጀምሮ አስከ ቀን 12/06/2017 ዓም ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ታክስ፣ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲሁም የመጫኛ እና ማውረጃ ወጪን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  10. ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና /ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ወይም አዳራሽ በቀን 12/06/2017 . ከቀኑ 800 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 830 ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 08 ወይም ኤጀንሲው አዳራሽ ይከፈታል።
  11. የጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
  12. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታ‏‏‎‏‏‏‎‏‏‏‏‎‏‎‏ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር - 058-222-1115/058-320-7769 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  14. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡

 

 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

ባህር ዳር

 

Save Tender