የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች ጎማ /Light and Heavy Vehicle Tyre/ እና ሞተር ሳይክል ጎማ /MotorBike Tyre/ ግዥ እና የእስቴሽነሪ /Stationary/ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/ኤ/አ/ብሔ/ግ/ጨ/002/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች ጎማ /Light and Heavy Vehicle Tyre/ እና ሞተር ሳይክል ጎማ /MotorBike Tyre/ ግዥ እና የእስቴሽነሪ /Stationary/ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
|
ሎት-1 |
የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች ጎማ /Light and Heavy Vehicle Tyre/ እና ሞተር ሳይክል ጎማ /MotorBike/ ግዥ |
የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም |
የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም 8:30 ሰዓት |
ብር 160,760.00 (አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ብር) |
|
ሎት-2 |
የተለያዩ የቢሮ መገልገያ የፅህፈት መሳሪያዎች /Stationary/ |
የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም |
የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም 8:30 ሰዓት |
ብር 58,190.00 (ሃምሳ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ዘጠኝ ብር) |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ ላይ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ) ለእያንዳንዱ ማለትም ሎት-1 እና ሎት-2 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር (1000254843017 EEU Ambo trict Connection Fee) በሚለው በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ ፡- አምቦ ከተማ ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር-- የድሮ ሃዮሜ ኮሌጅ ህንፃ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የአቅርቦት ሰንሰለት እና ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ «ኦሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ብሔ/ግ/ጨ/002/2017 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፣
- ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-112-609777/0912059263 መደወል ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን
