Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-2-20-59-92
  • Website
  • Deadline25 Feb 2025, 2:00 PM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Textile, Garment & Leather

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በድርጅቱ የደንብ ልብስ ተጠቃሚ ሠራተኞች የደንብ ልብስ ለወንዶች ኮትና ሱሪ፣ ለሴቶች ኮትና ጉርድ እና ቱታና ካፖርት /ጋዋን/ ጨርቅ ከነ ስፌት እንዲሁም የተዘጋጀ ሸሚዝ፣ የወንድና የሴት አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ እና የሥራ ቦታ ደህንነት ጫማ ወይም ሴፍቲ ሹዝ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 0019/ግዢ/17 .

 

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በድርጅቱ የደንብ ልብስ ተጠቃሚ ሠራተኞች የደንብ ልብስ ለወንዶች ኮትና ሱሪ፣ ለሴቶች ኮትና ጉርድ እና ቱታና ካፖርት /ጋዋን/ ጨርቅ ከነ ስፌት እንዲሁም የተዘጋጀ ሸሚዝ፣ የወንድና የሴት አጭር ጉርድ ቆዳ ጫማ እና የሥራ ቦታ ደህንነት ጫማ ወይም ሴፍቲ ሹዝ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁም መሠረት፡-

    • ተጫራቶች በሥራ ዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የመንግስት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
    • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ (CPO) በደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ስም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
    • የጨረታው ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 በመክፈል ሀዋሣ ከተማ በሚገኘው በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
    • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በማንኛውም ማሸጊያ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ 15ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
    • የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ 15ኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 830 ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
    • ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር በሚመጡበት ወቅት የሚጫረቱባቸውን የደንብ ልብስ ናሙና በዓይነት ከጨረታ ሰነድ ጋር ይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ቀርቦ ቢገኝ ተጫራቹ ጨረታውን ከመሳተፍ ይታገዳል፡፡
    • ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው::
    • ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር 046-2-20-59-92/09-16-83-66-53

 

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት

 

Save Tender