በአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2017 በጀት አመት ከዚህ በታች በተለያዬ በምድብ (ሎት) የተከፋፈሉትን ዕቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግመ007/2017
በአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በ2017 በጀት አመት ከዚህ በታች በተለያዬ በምድብ (ሎት) የተከፋፈሉትን ዕቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-
|
ምድብ (ሎት) |
የዕቃው/አገልግሎት አይነት |
የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ምድብ 001 |
ለረጲ ደረቅ ቆሻሻ ማስወገድ አገልግሎት የሚውል ዶዘር ማሽን ኪራይ |
ብር 300.00 |
የ80,000.00 ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ |
|
ምድብ 002 |
ገረጋንቲና ቦልድ ድንጋይ |
ብር 300.00 |
የ150,000.00 ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ |
|
ምድብ 003 |
ለጋዝ ማስተንፈሻ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ ዕቃዎች |
ብር 300.00 |
የ20,000.00 ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ |
|
ምድብ 004 |
የዲጂታል ማስታወቂያ ቦርድ (ዲጂታል ሳይንኤጂ) |
ብር 300.00 |
የ20,000.00 ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ |
|
ምድብ 005 |
ሞንታርቦ ከእነአከሰሰሪው |
ብር 300.00 |
የ20,000.00 ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ |
|
ምድብ 006 |
መንገድ ዳር የሚተከል ደስት ቢን |
ብር 300.00 |
የ60,000.00 ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንከ ጋራንቲ |
|
ምድብ 007 |
የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች |
ብር 300.00 |
የ30,000.00 ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ |
|
ምድብ 008 |
የቀላል ተሽከርካሪ ጎማዎች እና አላቂ ዕቃዎች |
ብር 300.00 |
የ15,000.00 ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ |
ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዝርዝር መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣ ከዕዳ ነጻ ስለመሆናቸው ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT (15%)) ተመዝጋቢ የሆነ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፣
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ማሸነፉ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10 (አስር) በመቶ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚሰራና ሕጋዊ ዕውቅና ካለው ተቋም ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ በ15 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈፀም የሚችል፣
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ሰነድ) ኦርጅናልና ኮፒ፤ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለዬት ለየብቻው በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ሕጋዊ ማኅተምና ፊርማ በማድረግ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ግዥ ዳይሬክተር ቢሮ 10ኛ ወለል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰአት (ቅዳሜና እሑድን ሳይጨምር) በአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ 9ኛ ወለል በመገኘት የጨረታ ሰነዱን በብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
- ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገርግን ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ሕዝባዊ ወይም ኃይማኖታዊ በዓል ከሆነ ወይም ቅዳሜና እሑድ ከሆነ ሌላ ማስታወቂያ ማውጣት ሳያስፈልግ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይከፈታል፣ በምድብ 006 ፤ ምድብ 007 እና ምድብ 008 የተጠቀሱ ግዥዎች ቅድሚያ ናሙና/ሳምፕል/ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አከፋፈት ስርዓት ላይ በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታው አይስተጓጎልም፣
- ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ፒያሳ በተለምዶ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው 15 ቀበሌ ኢትዮ ሴራሚክስ ጎን (ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢቲ ታዎር (ዮናታን ቢቲ ፈርኒቸር ከሚገኝበት ሕንጻ) የመንግስት ግዥ ዳይሬክተር 10ኛ ወለል ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- 011 275 0002 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከ/አስተዳደር የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ
