Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-14-42
  • Website
  • Deadline08 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-08 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Textile, Garment & Leather

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚግኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለተለያዩ የሰራተኞች የደንብ ልብሶችን እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የሚውሉ መግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ /ቤት በከተማው መስተዳድር ስር ለሚግኙ ሴክተር /ቤቶች ለተለያዩ የሰራተኞች የደንብ ልብሶችን እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የሚውሉ መግዛት ይፈልጋል።

  1. የሰራተኛ የደንብ ልብሶች
  2. የኤሌክትሮኒክስ እና የአዳራሽ ውስጥ እስሪን ቃዎች

በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ :-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የዘመኑን ግብር ከፍለው ማጠናቀቃቸውንና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን /ቤት ማቅረብ አለባቸው
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም ሲፒኦ ባንክ በሂሳብ ቂጥር 1054551161211 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስ ወረቀት ያላቸው::
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻችው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ /ቤት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ለእያንዳንዱ ማስከበሪያ CPO ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ሲሆን በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
  9. ተጫራቾች ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኮፒና ኦረጅናሉን ለየብቻው ታሽጎ መቅረብ አለበት። ቴክኒካሉን ያልፉት ተወዳዳሪዎች ፋይናንሻላቸው ይከፈታል።
  10. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 16ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ 800 ሰዓት ተዘግቶ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ//ቤት ሶስተኛ ፎቅ ገዢ ፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም /ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. ማንኛውም የደንብ ልብስ ተወዳዳሪዎች ሳምፕል ወይም ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
  12. የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን እስከ አዳማ ከተማ ገንዘብ /ቤት መጋዘን ድረስ በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለባቸው::
  13. የጨረታ አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታውቂያ እና በስል እንደተገለፀ 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ /ቤት ጋር መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ ሲሆን 7.5 % በክፍያ ጊዜ የሚቀነስ ይሆናል።
  15. መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢው 20 ፐርንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት፡፡
  16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-2-11-14-42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ /ቤት

 

Save Tender