የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት አመት ሎት 1 የመኪና ጎማ ሎት 2- የአልጋ ፍራሽ ሎት 3- የጽህፈት መሳሪያ ሎት 4- ፈርኒቸር ሎት 5- ጀኔሬተር ሎት 6- የማጣቀሻ መጽሐፍት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2017 በጀት አመት ሎት 1 የመኪና ጎማ ሎት 2- የአልጋ ፍራሽ ሎት 3- የጽህፈት መሳሪያ ሎት 4- ፈርኒቸር ሎት 5- ጀኔሬተር ሎት 6- የማጣቀሻ መጽሐፍት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት:-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለ2017 በጀት የንግድ ሥራ ፈቃድ ያሳደሱ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- ለአቅራቢነት የተመዘገቡ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትን የሕጋዊነት ሰነዶች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ዕለት ኦርጅናል የሕጋዊነት ሰነዳቸውን ለማመሳከሪያነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የአልጋ ፍራሽ በጨረታ ያሸነፈ ተጫራች ያለተጨማሪ ወጭ እስከ ዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ሎት 1 እና ሎት 2- 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከሎት 3 እስከ ሎት 6-20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO)፣ (በጥሬ ገንዘብ) ወይም በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት (Unconditional BID BOND) ማስያዣ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ እስከ 15ኛው (አስራ አምስተኛው) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000038613263 በማስገባት እና የባንክን አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኝ በመቁረጥ ከዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው ደረሰኙን በማሳየት የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመሙላት ፣ የሕጋዊነት ሰነዶችን ፎቶ ግራፊክ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (BID Security) በማዘጋጀት እና በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ እላዩ ላይ ማህተም፣ አድራሻና ስም ጽፎ በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ተከታታይ 16ኛ (አስራ ስድስተኛው) ቀን 4፡00 ድረስ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘውትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛ (አስራ ስድስተኛው) ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓግልም፡፡
ማሳሰቢያ መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-881-3338 ጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ መደወል ይቻላል፡፡
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
