የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ለፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሉትን የብረታ ብረት ተረፈ-ምርቶችን እና ያገለገሉ ጋዜጣዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች
ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ፋብረካችን የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ለፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሉትን የብረታ ብረት ተረፈ-ምርቶችን እና ያገለገሉ ጋዜጣዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች ግለሰቦች ማስረጃቸውን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኩባንያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 በመውሰድ ይህ ማስታወቂ ያበጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 5፡30 ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትሹ ተወዳዳሪዎች አንዱን ኪሎ ግራም የምትገዙበትን ዋጋ በመግለጽ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በሲፒአ ወይም በባንክ ዋስትና ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ብትወደድ በህሩ አብርሃም ህንጻ 3ኛ ወለል በሚገኘው የኩባንያው ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታው አሸናፊ ድርጅት/ግለሰብ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የራሳቸውን ትራንስፖርት በማቅረብ ተረፈ-ምረቶቹን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የገዙትን ጥሬ ዕቃ የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ኩባንያው ሌላ ጨረታ በማውጣት የሚሸጥ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
ኩባንያው ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፣ 251-5522681/ 251-5522731
አዲስ አበባ
የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ
