የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ የመኪና ጎማዎች እና ብረታ ብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችና ብረታ ብረቶች
ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2017
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ የመኪና ጎማዎች እና ብረታ ብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ ፡-
-
የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላችሁ፣ የግብር ከፋይነት ያሟላችሁና የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፣
-
የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣
-
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይቻላል፡፡
-
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 40,000.00 /አርባ ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ማሰራት አለባቸው፡፡
-
የጨረታው አሸናፊ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
-
ተጫራቶች ንብረቶቹን ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቅጥር ግቢው በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች ንብረቱን ለመግዛት በሙሉም ሆነ በከፈል ዋጋ መሙላት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ዶክመንቶችን ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በጥንቃቄ በሰም ታሽጎ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ በኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል፡፡
-
ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
-
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይተላለፋል።
-
መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፈል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ቢድ ቦንድ ከሆነ 60 ቀን እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
ማስታወቂያው ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የሚጋበዝ ቢሆነም ሌሎች ማንኛውም ፈቃድ የሌለው ግለሰብ መወዳደር የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር- 0113300112
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
