ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት የሠራተኞች ሙሉ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 009/2017
ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት የሠራተኞች ሙሉ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
1ኛ. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ፣
2ኛ. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
4ኛ. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
5ኛ. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
6ኛ. በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው::
7ኛ. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር አምስት መቶ (500.00) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ) ወሎ ሰፈር በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 32 በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
8ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ያቀረቡትን ዋጋ 2% በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
9ኛ. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስረከቢያ ጊዜ መጥቀስ አለባቸው፡፡
10ኛ. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ድርጅቱ መጋዘን ድረስ ማድረስ አለባቸው።
11ኛ. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛው የሥራ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት (ከሰዓት) ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ 8፡00 (ከሰዓት) ታሽጎ 8፡30 (ከሰዓት) በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
12ኛ. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል
ብራና ማተሚያ ድርጅት
