የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለተለያዩ ክፍሎች ለህሙማን አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ከሚመለከታቸው አካላት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት ለተለያዩ ክፍሎች ለህሙማን አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ከሚመለከታቸው አካላት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
እነዚህም:-
-
ምድብ 1 - የመድኃኒት ሪ-ኤጀንት እና ሳፕላይስ ግዥ
-
ምድብ 2 - የህትመት ግዥ
-
ምድብ 3 - የልብስ ስፌት እቃዎች ግዥ
-
ምድብ 4- የተለያዩ የመኪና ጎማ፣ ቅባትና ሽቶ ግዥ
-
ምድብ 5 - የተለያዩ ሼልፎች ግዥ
-
ምድብ 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይዞ ለመግዛት እና ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ጨረታ የሚወዳደሩ ድርጅቶች ፡-
-
በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
-
የግብር ከፋይነት መለያ /TIN/CARD/ ሰርተፊኬት ያላቸው
-
አጠቃላይ የግዢ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺ ብር /በላይ ከሆነ አቅራቢው የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
-
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ - 3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውንና ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
አጠቃላይ ስለ ጨረታው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሆስፒታሉ ዋና ገ/ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት አቅርቦት የመድኃኒት፣ ሪኤጀንትና ሳፕላይስ 250,000.00 /ሁለት መቶ ሀምሳ ሺ ብር / ለህትመት 30,000.00 /ሰላሳ ሺ ብር / ለመኪና ጎማ፣ ቅባትና ሽቶ 10,000.00 /አስር ሺ/ ብር ሌሎች ግን ማንኛውንም ግብር እና ታክስ ጨምሮ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/፣ ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ዋናውን ደረሰኝ ከፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአማርኛ ቋንቋ ስርዝ ድልዝ ላይኖር በዋጋ ማቅረቢያው ቅፅ መሰረት የአንዱን ጠቅላላ ድምር ዋጋ በመሙላትና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ አስተዳደር ሕንፃ 4ኛ ፎቅ የግዥ አፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 9 /ዘጠኝ/ ለዚሁ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 16 ቀናት 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሳጥኑም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡15 ይታሸጋል፡፡
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዥ አፊሰሮች ቢሮ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል /ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
-
ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
-
በጨረታው የሚሳተፋ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ /ማብራሪያ/ ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 058 3205738/058222 0916 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ ፡- ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
ባህር-ዳር
ስልክ ቁጥር :-058-226-4412 0582220231 082220916, ፋክስ 058-226-44-12
የፈለገ ህይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
