Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ባህር ዳር
  • Address ባህር ዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0582221100
  • Website
  • Deadline18 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-04-18 00:00:00
  • Categories Vehicle tire

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ለማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያላቸውን ጎማ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ገመኮኤ/04/2017

 

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል ለማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያላቸውን ጎማ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ/ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
  5. የሚገዛው የማሽነሪና ተሽከርካሪ አገልግሎት የሚውል የተለያየ መጠን ያለው ጎማ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/በኤጀንሲው ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጂናል በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 09 ደረሰኝ በማስቆረጥ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን 26/07/2017 . ጀምሮ እስከ 10/08/2017 ዓም ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000012858586 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፤ ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500.000.00 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ/ ብር ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ(Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፌሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት/ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን 26/07/2017 ጀምሮ እስከ ቀን 10/08/2017 . ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ታክስ፣ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲሁም የመጫኛ እና ማውረጃ ወጪን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና /ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ወይም አዳራሽ 10/08/2017 . ከቀኑ 800 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 0830 ወይም ኤጀንሲ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  11. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  12. ኤጀንሲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-222-1115/058-320-7769 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  14. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ መሙያገፅ ላይ ፊርማና ማህተምማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡

 

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

ባህር ዳር

 

Save Tender