አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ምርት እና ተረፈ ምርቶች እና ሌሎች ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጅኦመብሬን ምርት እና የተለያዩ ተረፈ ምርቶች ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- APF/20/2017/Local
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ምርት እና ተረፈ ምርቶች ማለትም፡-
- ሎት 1 የጅኦመብሬን ሽት ምርት ውፍረቱ 0.5 ሚ.ሜ የሆነ፣
- ሎት 2 የእንጨት ጣውላ (ፓሌት ጣውላ)፣
- ሎት 3 የዩፒቪሲ ጥሬ ዕቃ መያዣ ካኪ ከረጢት፣
- ሎት 4. የHDPE ምርት ችብስ እና፣
- ሎት 5. ሌሎች ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ (መወዳደር) ይችላሉ፡፡
- ለ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN Certificate) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በተ.ቁ 1 ላይ የተገለፀውን የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የማይችሉ፣ ከሆኑ ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መንግስታዊ ተቋም የ2017 በጀት ዓመት ግብር ያልከፈለበትን ምክንያት እና በዚህ ጨረታ እንዲሳተፍ የሚፈቅድ ደብዳቤ ለፋብሪካው በመፃፍ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ከላይ በሎት 1 ከተገለፀው የጅኦመብሬን ሽት ምርት በስተቀር በሌሎች ሎቶች ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የንግድ ፈቃድ እና ሌሎች የሕጋዊነት ሠነዶችን ማቅረብ ሳይጠበቅበት በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተወዳዳሪ ድርጅቶች ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጨምሮ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ወይም በኢ-ሜይል (e-mail) አድራሻ amharapipefactory@gmail.com ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የሕጋዊነት ሠነዶቻቸውን የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችን ማስረጃዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 206 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ15ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- 15ኛው ቀን ሕዝባዊ በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረበውን የጆአመብሬን ምርት እና ተረፈ ምርቶችን በአካል በፋብሪካው አድራሻ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00-5፡00 ሰዓት ማየት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የውል ስምምነት ለመፈጸም በቅድሚያ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በፋብሪካው ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ 09-35-98-37-29/09-18-08-18-26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ
