መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰነድ ቁጥር:- 114
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ቁሳቁሶቹም፡-
- የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች (ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች፣ ፍሪጅ፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችና የውሃ ማጣሪያዎች)፤
- አሉሙኒየም ነክ ከሆኑ ግብዓቶች የተሠሩ ያገለገሉ አልጋዎች፣ በርና መስኮቶች፣ ሼልፎች፣ ፋይል ካቢኔቶች እና ቁርጥራጭ የአሉሚኒየም ስክራፖች፤
- የተለያዩ መጠን ዓይነት ያላቸው ያገለገሉ የእንጨትና የብረት ወንበሮች፤ ጠረጴዛዎችና የተሰባበሩ ጣውላዎች፤
- የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች ናቸው::
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነዱ በቁጥር 4 ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 90,000 (ዘጠና ሺህ ብር) ብቻ ከያዘ ሲፒኦ ጋር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 09-30-79-64-13 ወይንም 09-75-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
