የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ከጎዳና ለሚነሱ ዜጎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ (05/001- 002/2017)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ከጎዳና ለሚነሱ ዜጎች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎች ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው እቃ/ አገልግሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
|
ሎት 1 |
ፍራሽ፤ ብርድ ልብስ፤ አንሶላ፤ የተለያዩ አልባሳት እና ጫማዎች ግዢ |
100,000.00 CPO |
|
ሎት 2 |
የተለያዩ የፅዳት እቃዎች ግዢ |
50,000.00 CPO |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና የፋይናንስ መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በቢሮ አካውንት 1000009650559 በማስገባት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከቢሮው ክፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት ደረሰኝ በማስቆረጥ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቶች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ብቻ ሞልተው እና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ ኮፒና ዋና (ኦርጅናል) ሰነድ ብለው በ2 ፖስታ በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ከላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ታሽጐ በእሉቱ 4፡30 ሰዓት በቢሮው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቶች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ነው
- ተጫራቶች ናሙና ለሚጠየቅባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ ፡-
የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
አድራሻ፡- አ/አ/ከ/ሴ /ህ/ማ/ጉ/ቢሮ ደጃች ውቤ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ወደ አፍንጮ በር አደባባይ በሚወስደው መንገድ የስድስት ኪሎ/የፈረንሳይ ታክሲ መጫኛ አለፍ ብሎ ቢሮ ቁጥር 206 1888 ህንፃ ላይ 2ኛ ፎቅ ስ.ቁጥር 09 47 95 17 60/09 42 12 94 92
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናት
እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
