በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ለ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የሠራተኞች የደንብ አልባሳትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር-ESLSE/P&T/REQ/2025/35071
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ለ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ የሠራተኞች የደንብ አልባሳትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት-አስራ አራት፡- የደንብ አልባሳት ጨረታ ግዥ
በዚህም መሰረት፡-
- በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት የምስክር ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግሥት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልገሎት ድረ- ገፅ (web site) ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን የሚያሳይ (supplier list) የምስክር ወረቀት።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ ሥልጣን ካለው አካል የተሰጠ ማስረጃ (Valid tax clearance) ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ የሚመልሰው በድርጅቱ ድረ- ገጽ (www. ESLSE.COM) ላይ በERP SYSTEM በዋና መ/ቤት ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ብቻ (ከዚህ ቀደም ያልተመዘገቡ ከሆነ) በሚሰጣቸው መለያ ቁጥር መሰረት የሚሞሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ቀን እና ሰዓት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስያዣ ሲ.ፒ.ኦ 20,000 ብር (ከንግድ ባንክ ፤ ከህብረት ባንክ እና ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ብቻ) ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማዕከሉ የሚገባ ይሆናል።
- ለደንብ አልባሳቶች ግዥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በቅ/ጽ/ቤቱ ናሙና መቅረብ ግዴታ ነው፡፡
- ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በሰልክ ቁጥር 0221/062/94 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የሞጆ ሎጅስቲክስ ማዕከል
