የዲላ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በዲላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የፖሊስ አባላት የሌሊት የደንብ ልብስ ግዥ በቀረበው ዝርዝር መሠረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሌሊት አልባሳት የደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/2017
የዲላ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በዲላ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የፖሊስ አባላት የሌሊት የደንብ ልብስ ግዥ በቀረበው ዝርዝር መሠረት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በንግዱ ሥራ ዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ም/ወረቀት ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የአቅራቢነት ምዝገባ ም/ወረቀት ያለው
- የግብር ከፋይ ምዝ/ምስክር ወረቀት
- ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ በባንክ የተረጋገጠ የ30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር በመክፈል በጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 6 ቀርበው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ዘግይቶ የመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል 1 ኦርጅናል 2 ቴክኒካል ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ፋይናንሻል 1 ኦርጅናል እና 2 ፋይናንሻል ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በማሸግ በመጨረሻ ሁሉንም በአንድ እናት በኤንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ አድራሻችሁን በመሙላት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት
