በአሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ በጎተራ ተከማችቶ የሚገኘውን 3.000 /ሶስት ሺህ/ ኩንታል 3ኛ ደረጃ ብጣሪ ገብስ /ተረፈ ምርት/ ውል እንደተዋዋለ ሙሉ ክፍያውን በቅድሚያ ፈጽሞ በሃያ (20) ቀናት ውስጥ ሊያነሳ ለሚችል ገዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የ3ኛ ደረጃ ብጣሪ ገብስ ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- OACF-AMF/MBSM/01/2017
በአሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ በጎተራ ተከማችቶ የሚገኘውን 3.000 /ሶስት ሺህ/ ኩንታል 3ኛ ደረጃ ብጣሪ ገብስ /ተረፈ ምርት/ ውል እንደተዋዋለ ሙሉ ክፍያውን በቅድሚያ ፈጽሞ በሃያ (20) ቀናት ውስጥ ሊያነሳ ለሚችል ገዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎትና አቅም ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::
- ተጫራቾች የ2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በእህል ንግድ ወይንም የከብቶች መኖ በማዘጋጀት ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል/ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00- 6:00 ሰዓት ድረስ አሰላ-ቁሉምሳ በሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 051 ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወሰደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ከርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች በኤንቨሎፕ የታሸገ የጨረታ ሰነዳቸውን በአሰላ ብቅል ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 051 በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሰላ (ቁሉምሳ/ በሚገኘው የፋብሪካችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ጨረታ ሰነዳቸውን የሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልከ ቁጥር፡- 022-3-31-52-66 ወይም 022-3-31-81-97 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ
