Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃላ/የተ/ አሰላ ብቅል ፋብሪካ
  • Address አዲስ አበባ ከተማ ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወስደው መንገድ ላይ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፈዴሬሽን ሕንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ወይም አሰላ- ቁሉምሳ : ኢትዮጵያ, Phone: 09-65-65-04-81
  • Website
  • Deadline06 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-05-06 00:00:00
  • Categories Byproducts

በአሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ በጎተራ ተከማችቶ የሚገኘውን 3.000 /ሶስት ሺህ/ ኩንታል 3ኛ ደረጃ ብጣሪ ገብስ /ተረፈ ምርት/ ውል እንደተዋዋለ ሙሉ ክፍያውን በቅድሚያ ፈጽሞ በሃያ (20) ቀናት ውስጥ ሊያነሳ ለሚችል ገዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

3 ደረጃ ብጣሪ ገብስ ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- OACF-AMF/MBSM/01/2017

 

በአሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን /የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ በጎተራ ተከማችቶ የሚገኘውን 3.000 /ሶስት ሺህ/ ኩንታል 3 ደረጃ ብጣሪ ገብስ /ተረፈ ምርት/ ውል እንደተዋዋለ ሙሉ ከፍያውን በቅድሚያ ፈጽሞ በሃያ (20) ቀናት ውስጥ ሊያነሳ ለሚችል ገዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎትና አቅም ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው::

  1. ተጫራቾች 2017 . የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በእህል ንግድ ወይንም የከብቶች መኖ በማዘጋጀት ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በፋብሪካችን አካውንት በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ 1000257808697 ወይም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000043405229 በመክፈል/ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 200-600 ከሰዓት በኋላ 700-1000 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት 200- 6:00 ሰዓት ድረስ አሰላ-ቁሉምሳ በሚገኘው ፋብሪካችን ቢሮ ቁጥር 051 ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና /ቤት ከጀርመን አደባባይ ወደ ሚካኤል አደባባይ በሚወሰደው መንገድ ላይ ሚካኤል /ከርስቲያን አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 . 800 ሰዓት ድረስ በአየር ላይ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  6. ተጫራቾች በኤንቨሎፕ የታሸገ የጨረታ ሰነዳቸውን በአሰላ ብቅል ፋብሪካ ቢሮ ቁጥር 051 በተቀመጠው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. ጨረታው በዕለቱ ሚያዝያ 28 ቀን 2017 . 800 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 815 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሰላ (ቁሉምሳ/ በሚገኘው የፋብሪካችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ ጨረታ ሰነዳቸውን የሚያቀርቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  9. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልከ ቁጥር፡- 022-3-31-52-66 ወይም 022-3-31-81-97 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን /የተወሰነ አሰላ ብቅል ፋብሪካ

 

Save Tender