ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. የመኪና ጎማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የመኪና ጎማ ለመግዛት የወጣ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር-178/25/GS/PUR
- ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. የመኪና ጎማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት መጫረት ይችላል።
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የቲን ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ምዝገባ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ተጫራቾች የጎማዎቹን አይነት ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ሙለጌ ህንፃ ሰባተኛ ፎቅ በሚገኘው ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከቫት በፊት ከተጠቀሰው ዋጋ ላይ 5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም C.P.O. ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት አለባቸው::
- በጨረታ ሰነዱና በC.P.O ላይ የሚጠቀሰው የተጫራች ስም አንድ ዓይነት መሆን አለበት::
- ተጫራቾቹ የጨረታውን ሰነድ (ቴክኒካል እና ፋይናሻል) በተለያየ ፖስታ አሽገው፤ ፖስታው ላይ የተጫራቹን ስም ፤ ስልክ ቁጥርና የሚወዳደሩበትን የጨረታ አይነት በፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ሚያዚያ 20 ቀን 2017 ተከፍቶ ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል።
- ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ቶታልኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ.
ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ ክፍል
ሳሪስ መንገድ ቡና ቦርድ ፧ ሙለጌ ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ 011 465 3044 ወይም 011 466 8025
