የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች እና ዕቃዎችን ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- ECCGB/NCB/004/2017/25
- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች እና ዕቃዎችን ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በመንግሥት ግዥ አዋጅ እና መመሪያ በተገለጸው ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓት መሠረት የሚገዛቸው አገልግሎቶች እና ዕቃዎች እንዲሁም በእያንዳንዱ የአገልግሎትና ዕቃ የሚፈለግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የአገልግሎትና የዕቃ ሎት ቁጥሮች መሰረት በማድረግ ነው።
- ሎት 01 - ለተሽከርካሪ ጎማ የሚያስፈልገው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 50,000.00
- ሎት 02 - ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ኤሲ ባለ 18 ቢቲዩ የሚያስፈልገው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 60,000.00
- የግዥ ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆነ ተጫራች እና ከአገልግሎቱ እና ከዕቃዎች ጋር አግባብነት ያላቸው የ2017 በጀት ዓመት የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ታክስ ክሊራንስ እና በቅርቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት ዲክለር ያደረጉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል - በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርቡ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ የሎት ዓይነት ከፍለው የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 በተገለጸው አድራሻ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው ለእያንዳንዱ የሎት ምድብ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ የሚገባበት አድራሻ ፦ በአዲስ አበባ መሿለኪያ በይርጋ ኃይሌ ሕንፃ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ጉምሩክ ኮሚሽን 4ኛ ፎቅ በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይሆናል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0335590080/0335590286 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
